ኢትዮጵያ የማዕከላዊ
ኢትዮጵያ የስምጥ
ሸለቆን በተባበሩት
መንግሥታት የትምህርት፣
የሳይንስና የባህል
ድርጅት (UNESCO) የዓለም ጂኦፓርኮች
ዝርዝር ውስጥ
በማስመዝገብ የመጀመሪያዋን
ታሪካዊ የጂኦፓርክ
እውቅና አግኝታለች።
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንን በመመደብ፣ በማስተባበርና የተለያዩ ድጋፎችን ለጥናት ቡድኑ በማድረግ የዚህ ታላቅ ስኬት አካል በመሆኑ ላቅ ያለ ደስታ ይሰማዋል።
UNESCOን ጨምሮ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ የጥናት ቡድኑ አባላት ወራቤ ዩኒቨርሲቲን መጎብኘታቸው ይታወሳል።
ዩኒቨርሲቲው ለቱሪዝሙ ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ሀገራዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በቁርጠኝነት መስራቱን ይቀጥላልል።
ዕውቀት ለልህቀት
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ