የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መ/ር ሙሀባ ኑረዲን የስልጠናው ዓላማ የመምህራንን ሙያዊ ብቃትና የማስተማር ክህሎት ለማሳደግ፣ ዘመናዊና ተማሪን ማዕከል ያደረጉ የማስተማር ዘዴዎችን ለማስተዋወቅ እንዲሁም የትምህርት ጥራትን ማሻሻል መሆኑን ተናግረዋል።
ስልጠናው ብቁና ተወዳዳሪ መምህራንን በማፍራት የተማሪዎችን የመማር ውጤት ለማሻሻልና የዩኒቨርሲቲውን የትምህርት ልህቀት ለማጠናከር እንደሚያግዝም ገልጸዋል።
የዩኒቨርሲቲው ትምህርትና ስነ-ባህሪ ት/ቤት ዲን መ/ር ሱልጣን ሁልጫፎ በበኩላቸው በስልጠናው መምህራን የትምህርት አቀራረብ፣ የተማሪዎች ተሳትፎና የክፍል አመራር ላይ ያላቸውን እውቀትና ክህሎት እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲው የመምህራንን ቀጣይ ሙያዊ እድገት በማጠናከር የትምህርት ጥራትና ተቋማዊ ልህቀትን ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት ለማስቀጠል ስልጠናው አጋዥ መሆኑ ተገልጿል።
ዕውቀት ለልህቀት
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ