ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በ2018
በጀት ዓመት አመርቂ ስራዎችን ሰርቷል-ክቡር አቶ በቀለ መንገሻ
ሐምሌ 14፣
2018 (ወራ/ ዩ
/ህ /አ
/አ /ግ)
የዩኒቨርሲቲው ስራ
አመራር ቦርድ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና
የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ገምግሞ አጽድቋል።
የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በስትራቴጂክ
ጉዳዮች ስራ
አስፈጻሚው አቶ
ተማም አርጋው ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል። የዩኒቨርሲቲው ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ
በቀለ መንገሻ ዩኒቨርሲቲው
በበጀት ዓመቱ በሁሉም ዘርፎች የሰራቸው ስራዎች ስኬታማ መሆናቸውን ገልጸዋል። አለም አቀፍ ትስስርና የአጋርነት ስራዎች እንዲሁም ዲጂታላይዜሽን ላይ
የተሰሩ ውጤታማ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው
ተናግረዋል።
በየደረጃው በቡድን መንፈስ መሰራቱ ለተገኘው ውጤት ማሳያ መሆኑን ክቡር አቶ
በቀለ ጠቁመዋል።
የዩኒቨርሲቲው ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ ፕ/ር አርጋው አምበሉ በበኩላቸው በዩኒቨርሲቲው
ውጤታማ የሆኑ ቤተሙከራዎች
መደራጀታቸው የመማር ማስተማር ስራውን ውጤታማ ማድረግ ማስቻሉን ገልጸዋል።
የተለያዩ ሲስተሞችን በማበልጸግ ረገድም ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን አመላክተዋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል ዩኒቨርሲቲው በ2018
በጀት ዓመት በመማር ማስተማር፣ በምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎትና አስተዳደር ዘርፎች በብዙ ቁልፍ የውጤት አመልካቾች (KPIs) ላይ የላቀ አፈጸጸም ማስመዝገቡን ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎቶችን
ዲጂታላይዝ በማድረግ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑንና ዩኒቨርሲቲውን ማራኪና ምቹ የስራ ከባቢ በማድረግ ረገድ ውጤታማ ስራዎች መሠራታቸውን
ገልጸዋል። የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ የ2018
በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና
የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን ገምግሞ አጽድቋል።
ዕውቀት ለልህቀት
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ