የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል ሁለቱ ተቋማት ያላቸው የስራ ግንኙነት በአርዓያነት ሊጠቀስ የሚችል መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የወራቤ ማረሚያ ተቋም ከወራቤ ዩኒቨርሲቲ ጋር ለሰራው ስራ ምስጋና አቅርበዋል።
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በቀጣይም ከተቋሙ ጋር ህዝብንና ሀገር ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎችን መስራቱን እንደሚቀጥልም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የወራቤ ማረሚያ ተቋም ኃላፊ ኮማንደር አወል ሁሴን ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ከሚሰራው የአረንጓዴ አሻራ ልማት ስራ ልምድ ወስደን ችግኝ በማፍላት አሻራችንን ተቋሙ ላይ ማሳረፍ ችለናል ብለዋል።
ይህም ተግባር በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚፈጠርን የአየር መዛባት ከመከላከል በተጨማሪ የተቋማቱን ግንኙነት በማጠናከርና ታራሚዎች ማህበረሰቡን እንዲያገለግሉ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።
የወራቤ ማረሚያ ተቋም በቀጣይም በዩኒቨርሲቲው የሚሰሩ የአረንጓዴ ልማት ስራዎችንና ሌሎች ስራዎችንም መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮማንደር አወል ገልጸዋል።
በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የወራቤ ማረሚያ ተቋም አመራሮችና ታራሚዎች፣ የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማልና የማኔጅመንት አባላት፣ የካውንስል አባላት፣ የተማሪዎች ህብረት አመራሮች እንዲሁም የስልጤ ዞን መስማት የተሳናቸው ማስተማሪያ ማዕከል ሰብሳቢ አቶ ፈድሉ መሀመድ ተሳትፈዋል።
ዕውቀት ለልህቀት
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ