ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ለሜቄዶኒያ አረጋውያንና አእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

News news
2026-07-23 12:43:10

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ለሜቄዶኒያ አረጋውያንና አእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
ሐምሌ 14 2018 (ወራ/ / / / /) ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ለሜቄዶኒያ አረጋውያንና አእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
ዩኒቨርሲቲው የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ፈርኒቸር አልባሳትና የንጽህና መጠበቂያ ሳሙናና ሌሎች ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል።  የዩኒቨርሲቲው ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ በቀለ መንገሻ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በርካታ ዜጎችን ሰብስቦ እያኖረ ላለው ሜቄዶኒያ ድጋፍ ማድረጉ ከህዝቡ ጋር ያለው ቅርበት የተጠናከረ እንደሆነ ጠቋሚ መሆኑን ተናግረዋል።
የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት / ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል የተደረገው ድጋፍ የማህበረሰብ አገልግሎት አንዱ አካል መሆኑን ገልጸዋል።  የሜቄዶኒያ አረጋውያንና አእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል መስራችና ስራ አስኪያጅ ክቡር / ቢንያም በለጠ በበኩላቸው 9 በላይጧሪ የሌላቸው አረጋዊያንና ህሙማን ለሚያስተዳደረው ሜቄዶኒያ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ላደረገው ድጋፍ አመስግነው ሌሎችም እንዲደግፏቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ዕውቀት ለልህቀት
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ

 

photo_2026-07-21_14-46-28-(2)-367830.jpg photo_2026-07-21_14-46-28-950687.jpg photo_2026-07-21_14-46-29-(2)-278995.jpg photo_2026-07-21_14-46-29-(3)-397863.jpg photo_2026-07-21_14-46-29-739957.jpg