ዶ/ር ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል በወራቤ ከተማ አስተዳደር የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አካሄዱ

News news
2026-08-05 09:39:47

/ ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል በወራቤ ከተማ አስተዳደር የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አካሄዱ

ሐምሌ 29 2018 (ወራ/ / / / /) የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት / ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል ከማኔጅመንትና ከካውንስል አባላት ጋር በመሆን በወራቤ ከተማ አስተዳደር ዳጤ ወዚር 6 ቀበሌ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አካሂደዋል።

 የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት / ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚመጣን የአየር መዛባት ለመቋቋም በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ወራቤ ዩኒቨርሲቲ እንደ ሀገር እየተካሄደ በሚገኘው አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የሚጠበቅበትን ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብሩ በተጠናከረ ሁኔታ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።  የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት / ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል በወራቤ ከተማ አስተዳደር ለዳጤ ወዚር 6 ቀበሌ ነዋሪዎች ለምግብነት የሚያገለግሉ ችግኞችን አበርክተዋል።  በችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ ላይ ለምግብነትና ለደን የሚውሉ ችግኞች ተተክለዋል።


ዕውቀት ለልህቀት


ወራቤ ዩኒቨርሲቲ

 

ph1-812266.jpg ph2-452122.jpg ph3-734843.jpg ph4-993230.jpg ph5-548740.jpg ph6-830443.jpg ph7-581040.jpg ph8-974848.jpg