የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመደቡት ዶ/ር እሱባለው ጌትነት ከቀድሞው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር-ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል የስራ ርክክብ አደረጉ።

News news
2026-11-10 09:32:14

በትምህርት ሚኒስቴር የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ተደርገው የተመደቡት ዶ/ር እሱባለው ጌትነት ከቀድሞው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር-ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል የስራ ርክክብ አድርገዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር እሱባለው ጌትነት ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር በቅንጅት በመስራት ተቋሙን ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ በትኩረት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በትምህርቱ ዘርፍ የሚጠበቀው ውጤት የሚሳካው በጋራ ጥረትና ርብርብ በመሆኑ ለዚህ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አስፈላጊውን ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ወራቤ ዩኒቨርሲቲን በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ፕሬዚዳንቱ ተናገረዋል።

የስራ ርክክቡ በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና ተማሪዎች ልማት ዴስክ ኃላፊ አቶ በየነ ተዘራ እና በትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ የሱፍ አልዬ አማካይነት ተካሂዷል።

ዶ/ር ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል ባለፉት ዓመታት በዩኒቨርሲቲው የተሰሩ ስራዎችን አፈጻጸም ያቀረቡ ሲሆን ለዶ/ር እሱባለው ጌትነት በዩኒቨርሲቲ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን አስጎብኝተዋቸዋል።

ዶ/ር መሀመድ አወል የአካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት እና መ/ር ሬድዋን ሙደሲር የአስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመድበዋል።

 

ዕውቀት ለልህቀት

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ

2-591680.jpg 3-831778.jpg 4-163315.jpg 5-183492.jpg